=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በቀላሉ ባለባበሴ ምክኒያት እኔን ተመልክታችሁ ጭቁን ስትሉ ትጠሩኛላችሁ።
ከውስጤ ያለውን ሳታውቁ በኩራት የለበስኩትን ልብስ ትገመግማላችሁ።
አካሌ ለእናንተ እይታ አይደለም፤ለሰውነቴ ሳይሆን ለአይምሮየ ልታናግሩት ይገባል።
እኔ የወንድ ባሪያ ያላደለሁ አንድ ግለሰብ ነኝ።
ለፈጣሪየ ትአዛዝ ተገዥ ነኝ።በጣም የምጓጓለት እና የምመኘው የአሏህን ውዴታ ነው፤በልቤ ውስጥ ቃላቶቹን ይዣለሁ፤ድምፅም አለኝ እሰማለሁ።
"እናተ ሴቶች ሆይ በደንቆሮዎች እንዳትቸገሩ እራሳችሁን ሸፋፍኑ!!!"
ወንድ እንዴት መልበስ እንዳለብኝ የሚነግረኝ ሳይሆን ከአሏህ የሆነ የማከብረው እና ለትእዛዙም ተገዥ የምሆንለት ህግ ነው።
ጭቁን አንድ ነገር ነው፤እኔ ያላደለሁት፤በውነቱ ነፃነቴ የያዝኩት አለባበሴ ነው።ይህ ነፃነቴ ከብዙ አመት በፊት ኢስላም ላንችም ለኔም ሲላክ የተሰጠን ነፃነታችን ነው።
ይህ አለባበሴ በአንድ አሊም ወይም ሸኽ የተጣለብኝ ግዴታ ሳይሆን መለኮታዊ ትእዛዝ ነው።
እናም እህቶቼ ለአሏህ ትእዛዝ እራሳችነን ተገዥ እናድርግ ማንነታችነን እንጠብቅ።አሏህ ህይወታቸውን በቁርአን እና በሐዲስ ብቻ ከሚመሩት መካከል ያድርገን።አሚን!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|